እልል ያለ ሽልማት


 

እልል ላለ ሽልማት የታጫችሁት ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ!

ጊዜና ታሪክ እራሳቸውን የሚያኖሩበት፣ በከበሩ ድንጋዮች የታነጸ ውብ ሕንጻ ነው - ባህል ማለት። የከበሩ ድንጋዮች በዘመናት ሂደት ውስጥ ማንነታችውን ሳይለቁ ወሳኙን ለውጥ በማስተናገድ ለየት ብለው እንደሚያሸበርቁት ሁሉ ባህልም ሥር መሠረቱን ሳይለቅ ከአዳዲሱ ጋር እየተናበበ እና እየተዋሃደ የየዘመኑንም መልክ እያተመ ይጓዛል። እንዲህ በከበረ ድንጋይ ተምሳሌት ያዘጋጀነው ሽልማትም የምንጋራው ባህልና ታሪካችን ዘመናትን በጽናት የሚሻገር መሆኑን ይመሰክራል።



አቶ ፍቃዱ ዋሬ በሙዚቃ


ኢንዱስትሪ ዘርፍ የመጀመሪያው ዙር የእልል ያለ ሽልማት የህይወት ዘመን ተሸላሚ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
ባላቸው የስራ ዘመን ሙዚቃን አንዱ የጥበብ መንገድ አደጋጐ በመጠቀም የኢትዮጲያን ህብረ ብሄራዊ ባህሎች እና እሴቶች በሀገር ውስጥና ለተቀረው የዓለም ክፍል በማሳተምና በማከፋፈል ባህልንና ጥበብን በልዩነት እንዲፀባረቅ ፤ እንዲተዋወቅ እና እንዲጎለብት ስላደረጉ የእልል ያለ ሽልማት የህይወት ዘመን ተሸላሚ ሆኑ

Video Block
Double-click here to add a video by URL or embed code. Learn more

ባህል የትያትር እስትንፋስ ነው፡፡


ኪነ ጥበብን ተዋህደው የኢትዮጲያን ድንቅ እና ውብ ባህሎችን በሀገርም ውስጥና በዓለም ዙሪያ በልዩነት ያንጸባረቁ ፤ ያስተዋወቁ እና እንዲጎለብት በማደረጋቸው አርቲስት የሺ ተክለወልድ በኪነ ጥበብ/ ትያትር ዘርፍ የመጀመሪያው ዙር የእልል ያለ ሽልማት የህይወት ዘመን ተሸላሚ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ሁሌም እልል ባለ ባሕላዊ አለባበሳቸው የምናውቃቻው ጥንድ የጥበብ ባለሞያዎች፣ እንዲህ በተገኙበት ሁሉ የኢትዮጵያን ባሕል ስለሚያስተዋውቁ በልዩነት እልል ያለ ተለሸላሚ ሆነዋል! ከወዲሁ እንኳን ደስ አላችሁ ልንላቸው እንወዳለን።

Video Block
Double-click here to add a video by URL or embed code. Learn more

የዓመቱ እልል ያለ የሙዚቃ ቪዲዮ ሽልማት የማን የሚሆን ይመስላችኋል?

Video Block
Double-click here to add a video by URL or embed code. Learn more

የዓመቱ እልል ያለ ማስታወቂያ ሽልማት የማን የሚሆን ይመስላችኋል?


እልል ያለ ጥሪ እልል ላሉ የባህል አምባሳደሮች!

Are you above 21 years old?

Yes No